የታዳሽ ሀይል ውጤቶች ጊዜ ያመጣቸው ፍቱን የኤሌክትሪክ ሃይል አማራጮች ናቸው፡፡ ድርጅታችን የአረንጓዴ ሀይል ሰጪ ውጤቶችን በማቅረብ በሀገራችን ዘመናዊ የፈጠራ ውጤቶች እና ለሀገራችን ተስማሚ ሂሳብ ቆጣቢ እና ንጹህ ሃይል ለማቅረብ እየሰራ ይገኛል፡፡
ModernEth ሀይል ማከማቻ ዘመናዊ መፍትሄ በማቅረብ፣ በመግጠም እና በመከታተል ለመኖሪያ ቤቶችም ሆነ ለመስሪያ ቤቶች እንዲሁም ባልተቆራረጠ መብራት ሃይል ጥገኛ ለሆኑ አካላት ያልተቋረጠ እና አካባቢን በማይጎዳ መንገድ አገልግሎቱን ይሰጣል፡፡ ድርጅታችን ተጨማሪ ምርቶችንም ወደ ሃገራችን በማስገባት እና በማቅረብ በናፍጣ ነዳጅ ያለንን ጥገኝነት ለማስቀረት ዝግጅት ይዟል፡፡