ዋና ጎራዎች


ድርጅትዎን በነጻ ያስተዋውቁ!

ወደ ኢዜጋ ድረ ገጽ እንኻን በደህና መጡ! ይህ የድርጅቶች ማዉጫ የተዘጋጀው በኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉ ሁሉ ካምፓኒዎች ኢንዲመዘገቡ እና ስራቸውን እንዲያስተዋውቁ ነው፣ ማንኛውም ሰው ወይንም ካምፓኒ እዚህ ድረ ገጽ በነጻ መመዝገብ ይችላል፣ የድርጅቱ ዝርዝርም ማስገባት ይችላል፣ ክድርጅቶች ማውጫው ሌላ፣ ኢዘጋ የተለያዩ ገጾች አሉት - ዜና፣ መዝናኛ፣ ስራ፣ ሪል እስቴት፣ ማስተዋቅያ፣ የመሳሰሉት ድረ ገጾች አሉት ለበለጠ መረጃ ኢሜል በዚሁ አድራሻ ይላኩልን፡ contact@ezega.com, ወይንም በዚህ ስልክ ይደውሉልን፡ 0912-706091 እናመሰግናለን!


ኢትዮ ቴሌኮም

አዲስ አበባ
http://www.ethiotelecom.et/amharic/index.php
+251(0)116 632597
ፋክስ +251(0)116 632674
ፖ.ሳ.ቁ1047

ካለፉት 5 ዓመታት ዕቅድ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ መንግስት በትምህርት፣ በጤና እና በግብርና ላይ የሚሰጠውን ልዩ ትኩረት ግምት ውስጥ በማስገባት የቴሌኮም አገልግሎቱ ለልማቱ አጋዥ ኃይል በመሆን የሚኖረውን አስተዋፅኦ በመረዳት ዘርፉን በላቀ ደረጃ ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ታምኖበታል፡፡

በመሆኑም ኢትዮ ቴሌኮም የተፈጠረው በከፍተኛ ደረጃ በማደግ ላይ የሚገኘውን የሀገራችንን ቀጣይ ዕድገት መንግስት በቴሌኮም አገልግሎት ለመደገፍ ካለው ጽኑ ፍላጎትና ስሜት የመነጨ ነው፡፡

በመሆኑም ዘመናዊ የቴሌኮም የስራ ሂደት ትግበራ፣ አስተማማኝ ኔትዎርክና መሰረተ ልማት ዝርጋታ እንዲሁም ከፍተኛ ጥራት ያለው የቴሌኮም አገልግሎት ለደንበኞቻችን ለማቅረብ አቅደናል፡፡ ይህ ተልዕኳችን ሲሆን ሁሉም አይነት ተግባሮቻችንም የሚመነጩት ከተልዕኳችን ላይ ይሆናል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ከታዋቂ ዓለም አቀፍ ኦፕሬተሮች ጋር ተመሳሳይ አገልግሎት ሰጪ ተቋም ሆኖ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ መንግስት በአለም ታዋቂ ከሆነው የፍራንስ ቴሌኮም ኩባንያ ጋር ስምምነት አድርጓል፡፡ ስምምነቱ የኢትዮ ቴሌኮም የማኔጅመንት አቅምን ዓለምአቀፍ ዕውቅና ያለው የዕውቀት፣ ልምድና ክህሎት ሽግግር በማድረግ ለማሳደግ ያስችላል፡፡

ስለሆነም ዓለምአቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት የጥራት ደረጃዎችን ስናሟላ የሚከተሉትን እሴቶቻችንን(values) እንጠብቃለን ብለን እናምናለን፡፡

    የሀገራችንን በተለይም ደግሞ የደንበኞቻችንን የቴሌኮም ምኞት እና ፍላጎት ተገንዝበን በሚፈለገው ሁኔታ ለማሳካት እንተጋለን
    ኢትዮ ቴሌኮም ህልውናው የተመሰረተው ከደንበኞቻችን በሚገኘው ገቢ መሆኑን በመረዳት ለደንበኞቻችን ልዩ ክብር እንሰጣለን
    ሠራተኞቻችን ለካምፓኒያችን ጠቃሚ ሀብት መሆናቸውን ተገንዝበን ምቹ የስራ ቦታ በመፍጠር እንዲያድጉና እንዲሻሻሉ እናደርጋለን፡፡
    ከፍተኛ ደረጃ ያለው የስራ አፈጻጸም፣ ጥራት ያለው የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ፣ ተቋማዊ ልህቀት (Excellence) እና በሁሉም ዘርፎች ቀጣይነት ያለው ማሻሻያዎች እንዲኖሩ እንተጋለን
    የሚያጋጥሙንን ችግሮች ሁሉ በፅናት ለመቋቋም እንጥራለን
    ገቢያችንን ከምንም በላይ ለማሳደግ ማናቸውንም አይነት ጥረቶች እናደርጋለን
    በሁሉም ተግባሮቻችን ላይ ታማኝ ሆነን ለመገኘት ስነ-ምግባሩን የጠበቀ አሰራር እንከተላለን
    ለካምፓኒያችን ባለድርሻ አካላት በሙሉ ተጠያቂ(Accountable) እንሆናለን

ኢትዮ ቴሌኮም አስተማማኝ ኔትዎርክ ለማዳረስና የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ያቀደውን ግብ ለመምታት የተለያየ ደረጃ ያላቸውን የልማት ስልቶች (ስትራቴጂዎች) ቀይሷል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የኢንፎርሜሽን ሲስተሙን ለማሳደግና ለማጠናከር አቅዷል፡፡ ይህም በአገልግሎት አሰጣጡ ሂደት ላይ በሽያጭና መስመር በመክፈት (activation) ረገድ ይታይ የነበረውን የቅልጥፍና ችግር ይቀርፋል፡፡ በተጨማሪም ለደንበኞች ይበልጥ ተጨባጭና ተዓማኒ የሆነ መረጃ ለመስጠት ያስችላል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው የሰው ሃይል አስተዳደርም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ ይህም የደንበኞቹን ምኞትና ፍላጎት ለማሟላት የሚችል ብቁ የሰው ሃይል (ሰራተኛ) ለመፍጠር ያስችለዋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የጥራትና ቁጥጥር የስራ ሂደት ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ ይህም የስራ ጥራትና ቅልጥፍናን ይፈጥራል፡፡ እንዲሁም ደንበኞች የቴሌኮም አገልግሎቱን በቅርበት እንዲያገኙ ይረዳል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የተሻለ የሪሶርሲንግ እና ፋሲሊቲ የስራ ሂደት ይጀምራል፡፡ ይህም አገልግሎቱን ለደንበኞች በተቀላጠፈ መንገድ ለማድረስ ይረዳል፡፡ በተጨማሪም የጥገና ስራዎችንም ለማቀላጠፍና በደንበኞቹ ዘንድ ግልፅነትን (Transparency) ለማስፈን ይረዳል፡፡








በአቅራብያው የሚገኙ ተመሳሳይ ድርጅቶች


አዲሲንያ ሆቴል
አዲሲንያ ሆቴል አዲስ አበባ አሉ ከሚባሉ ምርጥ ሆቴሎች አንዱ ነው፣ በሰርቪስ፣ በጥራቱና በምቾቱ ተወዳዳሪ የሌለው ሆቴል ነው፣ ዛሬ ይምጡና ይጎብኙን! Tel: +251-11 662 3634, +251-11 662 3439, +251-11 869 5408 Email: info@addissiniahotel.com, reservation@addissiniahotel.com
http://www.addissiniahotel .com
የኢትዮጽያ አየር መንገድ
የኢትዮጽያ አየር መንገድ
http://www.ethiopianairlines.com/