አጭር መግለጫ
የአዋሽ ሸለቆ ለም ምድር ወይን ለማብቀል በሚያመች አፈር እና የአየር ንብረት የተባረከ ነው፡፡ይህ ለወይን እርሻ ፍፁም ምቹ የሆነ ምድር፣ በአመት ሁለት ጊዜ ምርት እንድንሰበስብ አስችሎናል፡፡
ታሪካችን
በኢትዮጲያ ከንግስት ሳባ ዘመን አስቀድሞ ሳይከለስ የመጣ የሚያኮራን የወይን ጠመቃ ባህል አለን፡፡
በ1948 የተመሰረተው አዋሽ ወይን በኢትዮጲያ ረጅም አመታትን ያስቆጠረ የወይን ፋብሪካ ነው፡፡ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በሃገሪቱ ውስጥ ተወዳጅ ከሚባሉ ምርቶች መካከል አንዱ ለመሆን ችለናል፣ እንዲሁም ከአገሪቱ ባህል ጋር የተዋሀድን የገበያ መሪዎች ሆነናል፡
በመስከረም 2005 ዓ.ም ኤት ማይልሰ ኃ.የተ.የግ.ሽ. የተባለ በአፍሪካ እድገት ላይ ያተኮረ የግል የገንዘብ ምንጭ እና ኢትዮጲያዊው የስራ ፈጣሪ ባለ ሀብት አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ የድርጅታችን ባለቤት ሆነዋል፡፡ ከዚያን ጊዜ አንስቶ የምርት ክፍሉን እና የምርት ጥራቱን ለማሳደግ ከፍተኛ ወጪ ወጥቷል፡፡
ንብረቶቻችን
የላይኛው አዋሽ ሸለቆ ከአዲስ አበባ በደቡብ ምስራቅ 180 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡በተመቻቸ አፈር እና የአየር ንብረት ወይን ለማብቀል ምቹ መሬት ነው፡፡
በመርቲ ጀጁ የሚገኘውን የወይን እርሻችንን በዚህ ስፍራ ያገኙታል፡፡ ከዚህ ሁነኛ ስፍራ ነው የወይን ዘለላዎቻችን በአዲስ አበባ ልደታ እና መካኒሳ አካባቢ ለሚገኑት ሁለቱ ፋብሪካዎቻችን ስምንት አይነት የወይን ምርቶቻችንን ለማምረት የሚደርሱት፡፡
ምርቶቻችን
- አዋሽ ዋይን
- አዋሽ፣ የድርጅቱን መጠሪያ የያዘ ምርት ሲሆን በተጨማሪም የድርጅታችንን ምርቶች ሽያጭ በአንደኝነት ይመራል፡፡ መካከለኛ እፍጋት እና ወርቃማ መልክ ያለው ይህ ወይን ለስለስ ያለ የሎሚ ጣዕምን ከኪዊ እና ሃባብ ጋር አቀላቅሎ አስደሳች እና አነቃቂ ጣዕምን ፈጥሯል፡፡ ይህ ወይን በሞቃት ቀን ከጓደኞች እና ከቤተሰብ ጋር ሆኖ ለመጠጣት ወይም ከቀላል ምግቦች እና መቆያ ምግቦች ጋር ፍጹም ተስማሚ ነው፡፡
- ጉደር ወይን
- ይህ ቀይ ወይን ስሙን ከዚህ በፊት ወይን ተክል ከነበረን ቦታ የወሰደው ሲሆን በጣም ተዋቂ ቀይ ወይን ነው፡፡ደረቅ፣ደማቅ ቀይ፣ የቡና ጣዕምን ከቸኮላት ጋራ በማዋሀድ የጠለቀ፣ የሚያረካ የወይን ገጠመኝን ይፈጥራል፡፡ ከክትፎ ጋር ወይም በማንኛውም ቀን ከስራ በኃላ ከምግብ በፊት የሚጠጣ ነው፡፡
- አክሱሚት ወይን
- አክሱሚት፤ በኢትዮጲያ በጣም ከሚከበሩ ታሪካዊ ቦታዎች በአንዱ የተሰየመ ሲሆን ባለ ረጅም ዕድሜ እና በጣም ታዋቂ ወይናችን ነው፡፡ ደማቅ ቀይ ሆኖ የቼሪ እና የገውዝ ጥቅሻን ከአስደሳች ጣፋጭነት ጋር አዋህዶ የያዘ ነው፡፡ ይህ ወይን ደስታን ለመጋራት፣ መስቀልም ይሁን የረጅም ሳምንት መጨረሻ ቀንን፣ ባጠቃላይ ማንኛውንም አይነት በዓል ለማክበር በጣም ተስማሚ ነው፡፡
- ከሚላ ወይን
- ነጩ ወይናችን ከሚላ በወሎ አነጋገር ቆንጆ ማለት ነው፡፡ እርካታን የሚሰጥ በመካከለኛ ጣፋጭነትን፤ በቅቤያማ ቫኒላ እና አልመንድ መሰረት ተደግፎ የተዘጋጀ ነው፡፡ ከአሳ፣ ፓስታ ወይም ለነጭ ወይን አፍቀሪዎች ራሱን ችሎ የሚቀርብ ነው፡፡
ሰዎቻችን
ለስኬታችን ተጠቃሽ ከምናደርጋቸው ምክንያቶች ውስጥ ለወይን ምቹ የእርሻ መሬት እና የአየር ንብረት ተጠቃሽ ቢሆኑም ዋናው እና ብቸኛው መሰረታዊ ነገር አብረውን የሚሰሩት ሰዎች ናቸው፡፡
የሰራተኞቻችን ችሎታ፣ እውቀት፣ እንክብካቤ እና ጉልበት አዋሽን ዛሬ ያለበት ደረጃ አድርሶታል፤ ማለትም የኢትዮጲያውያን ተመራጭ ወይን፡፡
ውለታቸውንም ለመመለስም የስልጠና እና የትምህርት ዕድሎችን በማመቻቸት ብቃታቸውን እንዲገነዘቡ እናደርጋለን፡፡ ምኞታችን ሰራተኞቻችንን በሙሉ በማሳደግ መነሳሳታቸውን ራሳቸውን እና ድርጅቱን ለማሻሻል እንዲጠቀሙበት ማድረግ ነው፡፡
የምንጥረው የሰራተኞቻችንን ህይወት እና ማህበረሰብ ለማሻሻል ነው፡፡